Monday, February 17, 2014

ኖሮ ያልታየ ሞቱ ያልታወቀ

By Daniel Tadese | February 17, 2014
Daniel Tadesse
Daniel Tadesse
እኤአ በ1991 ስልጣን የተቆናጠጠው አረመኔያዊው የወያኔ ስርዓት በ23 አመታት ውስጥ በዜጎች ላይ ይህ ነው የማይባል ኢ ሰብዓዊ ድርጊት በመፈፀምና የህዝቦች ቀንደኛ ጠላት በመሆን የስልጣን ዘመኑን በማርዘም ላይ ይገኛል:: በተለይም ከጊዜ ወደጊዜ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየከፋ የመጣው የጭካኔ ዘመቻ ከየትኛውም ጊዜ በላይ በመባባስ ላይ ይገኛል::
የስርዓቱ ባለስልጣናት የኦነግ አባል የሆኑትን ብቻ ሳይሆን ያልደገፋቸውን ያላጨበጨበላቸውን የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑትን ማሰር፣ ማፈን፣ አፍኖም ማሰቃየት፤ከዚያም ደብዛቸውን በማጥፋት መግደል፤ ሃብት ንብረታቸውን መውረስ፤ እነርሱን አስሮ ቤተሰቦቻቸውን ከ ህብረተሰቡ እንዲገለሉና ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ለሞራል ውድቀትና ድቀት እየዳረጉ እንደሚገኝ ለማንም ግልፅና የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይ ፀረ ሽብር በሚል ሽፋን አሻንጉሊቱ ፓርላማ ባወጣው አዋጅ ቁጥር 652/2001 ኦነግንና አንዳንድ የነፃነት ታጋይ ድርጅቶችን አሸባሪ ብሎ በመፈረጅ አባል ናቸው ተብለው ከሚጠረጠሩ ግን ዓባል መሆናቸው በይፋና በግልጽ ከማይታወቁ ሰዎች ጋር ሰላምታ መለዋወጥ፤ አብሮ መሄድ፤ ሻይ ቡና መገባበዝ፤ መመገብ ሰላምታ ያደረጉ ሰዎችንም የአሸባሪነት ሰለባ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ ሌላ ጊዜ በሰፊው እመለስበታለሁ፡፡ Read more…

No comments:

Post a Comment