Tuesday, August 5, 2014

የበረሃዉ ጥሪ ከተማሪዉ አንደበት

በጂቱለሚ | Hagayyaa 5, 2014
ብዕሬን ስነጠቅ ፤ እሮሮዉ ሲበዛ ጠመንጃዉ ትዝ አለኝ::
መልዕክት ለትግራዩ የወንበዴ ቡድን!
imagesእናቴ በተፈጥሮዋ ቻይና ርኅሩኅ ናት። ሰሞኑን ግን ከወትሮዋ በተለያ መልኩ ማልቀሱን አብዝተዋለች።  እናቴ ‘Abdii koo’ በሚትለዋ አጭር ሀረግ ብቻ ደስታዋን ፣ ሀዘኗን ፣ ስስትዋን ፣ ጥልቅ የእናትነት ፍቅሯን ፣ ተስፋዋን ፣ ምክሯን ፣ ግሳፄዋን ፣ድካሟን ፣ ብርታቷን… ሁሉ ነገሯን ትገልጻለች። በቤት ዉስጥ የምንኖረዉ ሁለታችን ብቻ ነን ። ማታ ማታ እቤት ዉስጥ ቁጭ ስንል እኔ TVዉ ላይ ሳፈጥ እሷ ደግሞ በTVዉ ግርጌ  በተንጠለጠሉ ፎቶዎች ላይ ዐይኗን ተክላ ታሰላስላለች። አንደኛዉ ፎቶ ያባቴ ሲሆን ሌሎቹ የዘመድአዝማድ ፎቶዎች ናቸዉ። እናቴ ከፎቶዎቹ መካከል አንደኛዉን አተኩራ ባየች ቁጥር ዕንባዋን መቆጣጠር ይሳናትና ወደ ጓዳ ገብታ ታለቅሳለች። ተመልሳ ትመጣና ደግሞ እንዳልከፋ ልታረሳሳኝ ትጥራለች።
እንዳለመታደል ሆኖ ይህንን የናቴን መሪር ህይዋትና በቤተሰቤ ላይ የተጫነዉን አስከፊ ግጽታ ማጤን የጀመርኩት ገና ሕጻን እያለሁ ነበር። አባቴ በከተማዋ ስመጥር የህክምና ባለሙያ ነበሩ። በአንድ የመንግስት ሆስፒታል ዉስጥ ከሚሰጡት የህክምና አገልግሎት በተጨማሪ የግል ክሊኒክ ከፍተዉ በትርፍ ጊዜያቸዉ ለኀብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጣሉ። አገልግሎታቸዉ ከሞላጎደል የነጻ ያህል ስለሆና አንዳንዴ የህክምና ቁሳቁስ መግዣ ወጪዎችን ከራሳቸዉ ኪስ ለመሸፈን ይገደዳሉ። እናም ቤተሰቡ ለክፉ ቀን እንኳ የሚሆን የመጠባበቂያ ገንዘብ የለዉም ነበር። ሆኖም ግን ቤተሰቡ በእጅጉ ደስተኛ ነዉ ማለት ይቻላል። Read more… 
     
sorus  http://ayyaantuu.com/?option=com_content&view=frontpage 

No comments:

Post a Comment