By Daniel Tadesse | November 1, 2014
ሃገራችንና ወገኖቻችን ለኢኮኖሚና ማሕበራዊ ችግሮች ከመጋለጥ አልፈው አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ ናቸው ፡፡ ለሕዝቡና ለሀገሪቱ ጥቅም የሚቆም ብቃት ያለው አስተዳደር የለም፡፡ ህግ አለ ህገ መንግስት አለ ቢባልም ተገቢ ያልሆኑና ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚቃረኑ አፋኝ፣ አስደንጋጭ እና ኢሰብአዊ ሕጐችና ደንቦች በተከታታይ ይወጣሉ፡፡ እነኚህም ሕዝቡን በተደራራቢነት እያስጨነቁት ይገኛሉ፡፡ ህጐችና ደንቦች ሲወጡ ሕዝብ መወያየትና መምከር ሲገባው ውይይት ሳይደረግባቸው በዘፈቀደ እና ባልሰለጠኑ የመንግስት ካድሬዎች ተግባራዊ ሲሆኑ ይታያል፡፡
የወጡና የፀደቁ ሕጐች ላይም ሆነ በአፈፃፀም ላይ ችግሮች ሲፈጠሩ ማየት የሚኖርበት ፍርድ ቤት ነበር፤ ነገር ግን በሚወጡ ሕጐች የፍ/ቤት ሥልጣን ተነጥቆ ለኤጀንሲዎችና ለባለስልጣናት እንዲሁም ለሌሎች ባልበሰሉ ካድሬዎች ለተሞሉ መስሪያ ቤቶች እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ ከዚህ አኳያ ስናይ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ህዝባችን አግኝቷል ወይ? የሚል ጥያቄን አስነስቶ ከመሰላቸታችን የተነሳ በኢትዮጵያ ሕግና መንግስት እንደሌለ ለማንም ግልጽ ነው። Read more…
No comments:
Post a Comment